Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 208 የሱስ ባንተ ድኜ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ ባንተ ድኜ
ገንዘብህም ሁኜ
ባንተ ጻድቅ ነኝ
ግን በዓለም ነገር
ልቤ እንዳይታሰር
አንተ ጠብቀኝ።
፪፡ ክፉው ጠላቴ
ወጥመድ ለጥፋቴ
ዘርግቶብኛል።
በኔ ሲቀናብኝ
ሀብቴንም ሊነጥቅብኝ
ዞትር ያደፍጣል።
፫፡ ስለዚህ ወደኛ
አንተ ቸር እረኛ
ናና ጠብቀን።
ታናሽ መንጋህንም
ጋርደን አድነንም
ተንከባከበን።
