Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 206 የሱስ ሆይ አትለፍብኝ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ ሆይ አትለፍብኝ
ጸሎቴን ስማ፤
ሕዝብህ ጸጋህን ሲያገኝ
አትለፍብኝ።
የሱስ ክርስቶስ ጸሎቴን ስማ
ሕዝብህ ጸጋህን ሲያገኝ
አትለፍብኝ።
፪፡ አሁን ወደ ጸጋህ ዙፋን
እቀርባለሁ፤
ይቅርታህን ለመቀበል
እርዳኝ አቤቱ
የሱስ ክርስቶስ . . .።
፫፡ ስለ ቸርነትህ ብቻ
ጸጋህን ስጠኝ፤
የቆሰለ ልቤን ፈውስ
ቶሎ አድነኝ።
የሱስ ክርስቶስ . . .።
፬፡ አንተ ነህ የደስታ ምንጭም
ሕይወት አንተ ነህ፤
በሰማይና በምድር
ሌላ የለኝም።
የሱስ ክርስቶስ . . .።
