Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 205 ጌታ ሊከብር በሁሉ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ጌታ ሊከበር በሁሉ
ቅዱስ ቃሉ ይስፋፋል
ዘመናት ሲለዋወጡ
እንደ ጸና ይኖራል።
ከዓለምም ህዝቦች ሁሉ
ያምላክን ስም ይጠራሉ
ለልጁም ይሰግዳሉ።
፪፡ ወላጆችም ሕፃናትን
ወዳንተ ያቀርባሉ
በደስታ ቀን የረሱህም
ሲጨንቃቸው ይሹሃል።
በመከራ በኀዘንም
ኃይልን አጥቶ ለሚደክም
ሌላ ረድኤት አይገኝም።
፫፡ በሞት በሕይወት የሱስ ሁን
ዞትር ባጠገባችን
መንፈስ ቅዱስን ላክልን
መጽናናትን እንዲሰጠን።
በድካማችን ኃይል ሁነን
የሞትም ቀን ሲደርስብን
በምሕረትህ አበርታን።
