Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 203 ነፍሴ ሆይ አምላክን ባርኪ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ነፍሴ ሆይ አምላክን ባርኪ
ኃጢአትሽን ሁሉ ተወልሽ
ምስጋናውንም አትርሺ
ሕይወትሽን ክውጥፋት ተበጅሽ።
፪፡ ደዌሽን ሀሉ ፈወሰሽ
በጸጋውና በምሕረቱ
ከዘላለም ሞት ከለለሽ
እንድትኖሪ ለክብሩ።
፫፡ ያንቺ ሕይወት እንዲታደስ
በጎ ነገር አጠገበሽ
ቀድሶ በመንፈስ ቅዱስ
ወደ ሰማይ ክብሩ አስገባሽ።
፬፡ በምሕረቱ ደስ ይበልሽ
በጽድቅና በፍርድ ጠርቶሻል
በታላቅ ደስታ ሊያኖርሽ
አንድ ልጁን ቤዛ ሰጥቶሻል።
፭፡ ኃዘንና ጭንቀትን
በሥቃይ አጥፍቶልሻል
ሠውቶልሻል ሕይወቱን
ቅዱስ ደሙን አፍስሶልሻል።
፮፡ እንግዲህ አትጨነቂም
አምላክሽ ከአንቺ ጋራ ነው
መከራ አይደርስብሽም
እርሱ አዳኖሻል በጸጋው።