Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 20 በቤተ ልሔም በረት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 20 በቤተ ልሔም በረት የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ በቤተ ልሔም በረት
ግሩም ነገር አይተናል።
የአምላካችን ምሕረት
አሁን ጐብኝቶናል።
በዳዊት አገር መድኅን
ዛሬ ተወለደልን
እርሱም ክርስቶስ ጌታ።
፪፡ በበረት ውስጥ የተኛው
ሕፃን ጌታችን ነው።
ተወለደ እንደኛ
እንዳብ ግን አምላክ ነው።
የምድር አሕዛብ ሁሉ
ለእርሱ ይሰግዳሉ
በቃሉ ታምነው።
፫፡ እኛም እንደ መልአኩ
ከልብ እናመስግን።
አብ ወልድን በመላኩ
ደኅንነት ሆነልን።
ለአምላክ ይሁን ክብር
ሰላም በዚህ ምድር
ለሰውም በጎ ፈቃድ።

Exit mobile version