Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 199 ሰንሰለትን መስበር የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ሰንሰለትን መስበር
የሚችል ማን ነው?
ነፃነት ፈጣሪ
የሱስ ብቻ ነው።
ወደ አንተ ጌታ እቀርባለሁ፤
ባርነቴም ቀረ ልጅህ ሆኛለሁ።
ያንተ ነኝ ኦ የሱስ፥ ያንተ ነኝ፥
ያንተ ነኝ
ሙሉ ተስፋ አለኝ የሱስ በደምህ።
፪፡ በመንፈስህ እርዳኝ
ቸር እረኛዬ፤
በመንገድህ ምራኝ
ወደ ሀገሬ።
መስቀልህ ይበቃል ለሙሉ ሕይወት
ለሁሉ ይሰጣል ጽኑ ሃይማኖት።
ያንተ ነኝ . . .።
፫፡ ከሰይጣንም ጭንቀት
ፍጹም ወጣሁ፤
ወደ ክርስቶስ ሕይወት
መጥቼአለሁ።
ሌሎች እንዲያዩ ያምላክን ደስታ፥
እጠራቸዋለሁ ባንተ ስም ጌታ።
ያንተ ነኝ . . .።