Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 198 የምሥራች ሰምተናል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 198 የምሥራች ሰምተናል የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የምሥራች ሰምተናል፤
ኢየሱስ ያድናል።
ታሪኩን ተናገሩ፤
ኢየሱስ ያድናል።
ወንጌልን አሰራጩ፤
መከራን ሁሉ ቻሉ።
የጌታችን ፈቃድ ነው፤
ሰው ሁሉ እንዲድን።
፪፡ ታላቅ ጸጋ ተሰጠን፤
ኢየሱስ ያድናል።
ደስ ይበላችሁ ኃጢአን፤
ኢየሱስ ያድናል።
ልባችሁን ክፈቱ፤
የሱስንም አስገቡት።
ለሰይጣን ስፍራ ንሱት፤
ጌታ እንዲነግሥ።
፫፡ ዙፋኑን ትቶ ወርዷል፤
ኢየሱስ ያድናል።
በሞቱ ሕይወት ሰጠን፤
ኢየሱስ ያድናል።
ደስ ብሏችሁ ዘምሩ፤
ለአምላክ ልጅ ለበጉ።
ድል ስለ ተገኘልን፥
እንዘምር ለአምላክ።
፬፡ ሃሌ ሉያ እንበል፤
ኢየሱስ ያድናል።
ሕዝቦች ደስ ይበላችሁ፡
ኢየሱስ ያድናል።
በደሙ ዛሬ ገዛን፤
ወደርሱ እንድንቀርብ።
ምሕረትን እንድንወስድ፥
ጸጋን እንድናገኝ።

Exit mobile version