Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 189 ጠውልጎ እንደ አበባ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ጠውለወጎ እንደ አበባ
ቀሪ ነው ያለም ተስፋ።
ግን፥ ሕያው ምንጭ ፈልቆልናል፤
ነፍሳቸንን
ከጥማት የሚያረካ።
፪፡ ወልድ ታላቅ ፍቅሩን አሳየን፤
የሕይወት ምንጭ ሆነልን።
በደሙ እኛን ሊዋጀን፤
ለነፍሳችን ሕይወቱን ለወጠልን።
፫፡ በኃጢአት የወደቀውን፥
የሱስ ማንሣት ይወዳል።
ሙሉ ይቅርታ ሊሰጠው
ሊያድነውም፥
በቃሉ ይጠራዋል።
፬፡ የሱስ መንገድ ሆኖልናል፣
ሊመራን ወደ ሕይወት።
የፈለገ ያገኘዋል፥
ይሰጠዋል።
ለለመነው በእምነት።
፭፡ በግሩም ቃሉ ይመራናል፥
መጽናናት እየሰጠን።
ሁልጊዜ ይጠብቀናል፥
ይምረናል፥
እንደ ምሕረቱ መጠን።
፮፡ በጎ እረኛ ሆኖአል፥
የሚጠብቅ መንጋ።
ቅዱስ ቁርባን ሠርቶልናል።
ሰጥቶናልም፥
ሥጋውንና ደሙን።
፯፡ከኵነኔሊ ሊያድነን፥
ሕይወቱን ለወጠልን።
በጭንቀታችን ሊደግፈን
ሊነዳንም፥
ኃይልና ብርታት ሆነን።
፰፡ አምላክ ሆይ በቅዱስ ቃል
ጽኑ እምነትን ስጠን።
እኛን ልጆች እድርገን፥
በምሕረትህ
በጉዞአችን ምራን።
፱፡ ከሥቃይ የምታድነን፥
አምላካችን አንተ ነህ።
በመከራና በኀዘን
ልትረዳን
ለኛ ጸጋህን ስጠን።