Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 188 አመስግኑት ክርስቶስን መድኃኒታችን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አመስግኑት ክርስቶስን መድኃኒታችን፤
ዘምሩለት ፍቅሩንም አስታውቁ፤
አመስግኑት ክርስቶስን የጥንት አምባችን፤
ክብር ሁሉ ይሁንለት ለርሱ።
የሱስ ነውና ቸሩ ጠባቂያችን፤
በክንዱ ይሸከመናል እርሱ።
አመስግኑት ታላቅ ነው መድኃኒታችን።
አመስግኑ የሱስን አክብሩ።
፪፡ አመስግኑት ክርስቶስን መድኃኒታችን፤
ለእኛ ሲል ደሙን አፈሰሰ።
አምላካችን ነው ተስፋችን መጠጊያችን፤
ይንገሥ፥ ይንገሥ ሞትን ያሸነፈ።
ስገዱለት እርሱ ነው ንጉሣችን፤
ታላቅ ፍቅሩን ለኛ የገለጠ።
አመስግኑት ታላቅ ነው መድኃኒታችን።
ክብር ይሁን ከሞት ለአዳነን።
፫፡ አመስግኑት ክርስቶስን መድኃኒታችን፤
አዲስ ቅዱስ ቅኔ ተቀኙለት።
ጌታ የሱስ ይንገሥልን በልባችን፤
ይንገሥ፥ ይንገሥ ለርሱ ይሁን ስብሐት።
ሊመጣ ነው ሊቀ ካህናት ጌታችን፤
ክብር ኃይልም ለርሱ ይሁንለት።
አመስግኑት ታላቅ ነው መድኃኒታችን።
አመስግኑ የሱስን አክብሩ።
