Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 185 ጸሎቴን ስለ ሰማልኝ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ጸሎቴን ስለ ሰማልኝ፥
አምላኬን ልወድስ ነኝ።
ረጆቼ ሁሉ ሲተዉኝ፥
ጌታዬ ረደኤት ሆነኝ።
ክፉውን ሁሉ ድል ነሣልኝ፤
ኃጢአቴን ይቅር አለኝ።
፪፡ በሕይወት፥ በሞትም ጊዜ፥
ተስፋ አለኝ ባምላኬ።
እርሱ ረዳኝ በጭንቀቴ፥
ስለዚህ ተደስቼ፥
የሱስ ጌታዬን ላመስግን፥
ልዘምር ለዓለም መድኅን።
