Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 179 ሰማያት የአምላክን ክብር የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ሰማያት የአምላክን ክብር
ይናገራሉ።
ፍጥረታት ሁሉ የጆቹን ሥራ
ያወራሉ።
ቀንም ለቀን
ታወጣለች ነገርን
ትናገራለች እውቀትን።
፪፡ እርሱ እንደሙሽራ
ከእልፍኙ ይወጣል፤
እንደ ኃያል በመንገዱ
ለመሮጥ ደስ ይለዋል።
አወጣጡ
ከሰማይ ዳርቻ ነው
ዙረቱም እስከ ዳርቻው።
፫፡ የአምላክ ሕግ ፍጹም ነው
ነፍስን ይመልሳታል፤ ሕፃናትንም
በሙሉ ጠቢባን ያደርጋል።
ያምላክ ሥርዓት
ቅን ነው፤ ልብን ደስ ያሰኛል
ትእዛዙ ዓይንን ያበራል።
፬፡ ያምላክ ፍርሃት ንጹሕ ነው
ለዘላለም ይኖራል
ፍርዱም እውነትና ቅንነት
በአንድነት ነው።
ከጠራ ወርቅ
ከእንቍም ይወደዳል
ከማር ይልቅ ይጣፍጣል።
፭፡ የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ
ባርያህን ጠብቅ፤
የዚያን ጊዜ ከታላቁ ኃጢአት
እነፃለሁ።
መድኃኒቴ፥
አቤቱ የአፌ ቃል
በፊትህ ያማረ ይሁን።
