Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 178 የኔ ነህ የሱስ ሆይ እወድሃለሁ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የኔ ነህ የሱስ ሆይ እወድሃለሁ፤
ስላንተ ያለምን ደስታ ትቻለሁ።
ቅዱስ አምላኬ ሆይ፣ ሁን መድኃኒቴ፤
እጅግ የምወድህ ቸሩ ወዳጄ።
፪፡ እኔ የምወድህ ብትወደኝ ነው፤
ነጻነቴን በክቡር ደምህ ገዛኸው።
ስላደረግክልኝ ተመስገን ጌታዬ፤
እጅግ የምወድህ ቸሩ ወዳጄ።
፫፡ በሕይወት በሞትም እወድሃለሁ፤
ትንፋሽ ካለኝ ደግሞ እወድሳለሁ።
በጠራኸኝ ቀንም እላለሁ አምላኬ፤
እጅግ የምወድህ ቸሩ ወዳጄ።
፬፡ በከበረ ስፍራ በማያልቅ ደስታ፤
ሳመሰግንህ ነው የነፍሴን ጌታ።
ዘውድ ደፍቼ ደግም ላይህ ነው የሱሴ፤
እጅግ የምወድህ ቸሩ ወዳጄ።
