Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 175 አምላክን አክብሩ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 175 አምላክን አክብሩ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ አምላክን አክብሩ
እሙን ነው ምክሩ
ይስፋ ክብሩ።
በኃይሉ ነግሦአል።
ጸጋን ለግሶልናል
እንዴት ያስደንቃል
ታላቅ ፍቅሩ።
፪፡ ተዋረደ ለሰው
ጽዋውም መረረው
ሲቀበለው።
አዳኛችን ሲሞት
መላእክት አደነቁት
መስቀሉም ሕይወት
ሊሰጠን ነው።
፫፡ ምሕረቱ ታላቅ ነው
ሊያመሰግነው
አይበቃም ሰው።
አንድ ቀን ግን በሰማይ
ግርማውን በግልጥ ስናይ
ምስጋናው እንደ ባሕር
ያስተጋባል።

Exit mobile version