Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 173 ኃይሉ ባንተ የሆነ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 173 ኃይሉ ባንተ የሆነ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ኃይሉ ባንተ የሆነ
በእውነትም ምስጉን ነው።
በአንተም የታመነ
ታላቅ ሕይወት አለው።
ክብር ትሰጠዋለህ፤
አያፍርም በመንግሥትህ፤
ኦ እግዚአብሔር።
፪፡ ልጅህን ለሞት ሰጠህ፤
የጠፋውን ዓለም
ልትቀድሰው በጸጋህ።
ሁሉ በልጅህ ደም
ከኃጢአት ነጽቶአል፤
ፍጹም ተፍቆለታል
ጽድቅ አጐናጸፍኸው።
፫፡ በጸጋህ የሚያምኑ
በሰማይ አያፍሩም።
መንግሥትን ይወርሳሉ፤
ደስታቸው አያልቅም።
እንባቸውን ራስህ
ትጠርግላቸዋለህ፤
ዳግም አያለቅሱም።
፬፡ ሥቃይና መከራ
አይደርስባቸውም፤
መላው የጸጋህ ሥራ
ሆኖአቸዋል ፍጹም
የዘላለም ዕረፍት
በሰጠሃቸው ሕይወት፥
ጽድቃቸው አንተ ነህ።

Exit mobile version