Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 169 ሕዝቦች ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 169 ሕዝቦች ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ሕዝቦች ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፥
አምላክን አመስግኑ።
በኪዳኑ የቆማችሁ፥
በአንድነት ቅረቡ።
ቅረቡ በእልልታ፥
ዘምሩ ለቸር ጌታ።
፪፡ ዘምሩለት በደጆቹ፥
አምልኩት በመቅደሱ።
ካገር ሁሉ ተከማቹ፥
ቸሩን ጌታ ወድሱ፤
ርኅሩኅ ሆኖ ይጸናል።
ሁልጊዜም ይመራናል።
፫፡ እርሱ ነው የፈጠረነ፤
መድኅን የላከልነ።
ከዘላለም ፍርድ ያዳነነ፥
ጽድቅን ያጎናጸፈን።
ለሰማያዊው ደስታ፥
ሆኖልናል አለኝታ።

Exit mobile version