Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 153 የሕይወትን ምንጭ አየሁ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሕይወትን ምንጭ አየሁ፤
ሲወጣ ክጐኑ።
በየሱስ ደም የታጠቡ፥
ከኃጢአት ይነፃሉ።
፪፡ ያ ሕያው ምንጭ ያነፃኛል
ከሠራሁት በደል።
እቀበላለሁ በምሕረት፤
የኃጢአቴን ስርየት።
፫፡ ያንን ምንጭ ካየሁ በእምነት፥
እድናለሁ ከሞት።
አምላክ በፍቅሩ ብቻ ነው፥
ሰውን ሁሉ ያዳነው።
፬፡ በሰማያት አዲስ መዝሙር
ልዘምር ለርሱ ክብር።
ላነፃኝ በምሕረቱ
ላገባኝ በቤቱ።