Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 151 የጥንት አምባ ጥግ ሁነኝ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የጥንት አምባ ጥግ ሁነኝ፥
ከለላህ ይሠውረኝ፤
ከተወጋው ጐንህም
የወጣው ውኃና ደም
ከክፋቴ ይጠበኝ፤
ከጥፋትም ያድነኝ።
፪፡ ሕግህን መፈጸሙ
አቅቶኝ ተሸነፍሁ፤
ሌትም ቀንም አልቅሼ
አልጠራልኝም እድፌ፥
አንተ ብቻ መድኅኔ
አድነኝ ከኵነኔ።
፫፡ የምሰጥህ የለኝም
ጽርቅ አልተገኘብኝም፤
አንተ ብቻ ጽድቅ ሁነኝ
ጸጋህ ብቻ ያድነኝ።
ቅዱስ ደምህ አምላኬ
ይሁንልኝ ሕይወቴ።
፬፡ የፍርድ ዕለት ሲደርስም
ምድራችን ሲፈርስም፥
ዓለም ካይንህ ፊት ሲቀልጥ
በግርማህ ስትገለጥ፥
ይጥንት አምባ ጥግ ሁነኝ
ከለላህ ይሠውረኝ።