Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 150 የሱስ ሆይ የሕይወት ውኃ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ ሆይ የሕይወት ውኃ
የጸጋ ምንጭ ሆንህልኝ።
የልቤን ልመና ስማ
በጸጋህ ፈጽምልኝ።
ታላቅ ፍቅርህ ግሩም ስምህም
የከፈልህልኝ ዕቅፍህም
ለነፍሴ ዕረፍት ሰጠ።
፪፡ የሱስ ሆይ ወደ መስቀልህ
እጄን እዘረጋለሁ።
ዓይኔንም ወደ ምሕረትህ
በተስፋ አነሣለሁ
የውድቀት ዛፍ ያፈራውን
በእንጨት መስቀል ተሰቅለህ
ፍጹም አጠፋህልኝ።
፫፡ ተመስገን ቸር መድኃኒቴ
ፍርዴን ተሸከምህልኝ።
በማይመረመር ርኅራኄ
ሞቴን ተቀበልህልኝ።
ዕዳዬን ሁሉ ከፈልኸው
ለኔ ሰማይን ከፈትኸው
ስምህን እንዳከብር።
፬፡ ዓይኔ ሲዘጋ፥ አካሌም
ወደ መሬት ሲመለስ፥
ከመከራ ከትካዜም
ድኜ አንተን ላመሰግን።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስም
ይሁን ምስጋና ውዳሴም
እሰከ ዘላለም አሜን።
