Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 145 እንዴት ያለ ድንቅ ለውጥ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ እንዴት ያለ ድንቅ ለውጥ በሕይወቴ ሆነ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የፈለግሁት ብርሃን በነፍሴ ውስጥ አለ፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የደስታ ጐርፍ በነፍሴ
እንደ ወንዝ ይፈሳል፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
፪፡ ከመኰብለልና ከጥፋት ድኛለሁ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
በዝተው ከነበሩት ኃጢአቶች ነጻሁኝ።
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
፫፡ የተረጋገጠ ጽኑ ተስፋ አለኝ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የጥርጥር ጭጋግ በመንገዴ የለም፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
፬፡ በሞት ሸለቆ ውስጥ ብርሃን በርቶልኛል
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የሰማይን ቤት ደጅ በሩቅ አየዋለሁ፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
፭፡ እሄዳለሁ ልኖር በሰማይ ከተማ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
በጣም ደስ ይለኛል ጉዞዬን ስቀጥል፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
