Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 143 አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 143 አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ
እኔ ጥፋተኛ ነኝ።
ያለ አንተ እጠፋለሁ
ያለ አንተ የሞትሁ ነኝ።
ቅዱስ ክቡር ደምህ ብቻ
ሊጠራኝ ይችላል።
ያንተ ጽድቅ ያንተ ይቅርታ
እኔንም ያጸድቀኛል።
፪፡ አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ
እኔ ራሴ ዕውር ነኝ
ዞትር እንከራተታለሁ
መንገዱን አላገኝም።
ና በእውነትህ ብርሃንም
እጄን ያዝና ምራኝ።
ባንተ ጽድቅና ሥልጣንም
ወደ መንግሥትህ አግባኝ።
፫፡ አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ
በዚህ ስደተኛ ነኝ።
ርስት በላይ ተቀብያለሁ
አንተ ራስህ ሰጠኸኝ።
ወደዚያ እጓዛለሁ
ጐርባጣው መንገዴ።
የሱስ ሆይ አንተን እሻለሁ
ኃይልህ ብቻ ኃይሌ ነው።
፬፡ አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ
በደለኛን የሚችል።
አንድ ወዳጅ እፈልጋለሁ
ክፉውንም የማይጥል።
አንተም ሰርክ ትወደኛለህ
ከቶ አትጥለኝም።
ጉድለቴንም ታውቀዋለህ
ፍቅርህ ግን አይተወኝም።
፭፡ አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ
በፈቃድህም ምራኝ።
መንፈስህንም እሻለሁ
እርሱን የሱስ ሆይ ስጠኝ።
እርሱ ትልቅ ኃጢአቴን
ሁሉ ቀን ያሳስበኝ።
እርሱም የስርየት ብዛትን
ባንተ ቃል ያስተምረኝ።
፮፡ በምድራዊ ሕይወት ሳለሁ
ሲያልቅብኝም ቀኔ።
አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ።
እንድድን ከኩነኔ
አንድ እርምጃ ለመራመድ
ያለ አንተ አልችልም።
ካንተ ጋራ ግን ብዛመድ
አንዳች አይጐድልብኝም።
፯፡ አንተን የሱስ ሆይ እሻለሁ
አንተ ብቻ ሀብቴ ነህ።
አንተንም አንድ ቀን አያለሁ
በአብ ቀኝ ተቀምጠህ።
ወደ ጽዮንም ተራራ
አድነህ ስታደርሰኝ።
በደምህ ከተዋጁት ጋር
ለክብርህ ልዘምር ነኝ።
ተ.ሲሞን ረስቲን

Exit mobile version