Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 141 ያለ ደስታ ስኖር ሳለሁ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ያለ ደስታ ስኖር ሳለሁ፥
የሱስ ደምህ ፈሰሰልኝ።
ምሕረትህን ልቀበል መጣሁ፤
የአምላክ በግ መጣሁ እርዳኝ።
፪፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን
ጊታዬ ሆይ፥ አውጣኝ እኔን።
ጊዜያቱ ሳያልፍብኝ፥
የአምላክ በግ ና አድነኝ።
፫፡ በምድር ተንገላትቼ፥
በችግርና በጭንቀት
እኖራለሁ ተዋርጄ።
ጌታ ሆይ፥ አውጣኝ ከጭንቀት።
፬፡ ቸሩ የሱስ ተቀበለኝ፤
ምሕረትህንም ስጠኝ።
በተስፋህ እንዳምን እርዳኝ፤
የአምላክ በግ መጣህ መጣሁ።
፭፡ በመስቀል ሞት የገዛኸኝ፥
ጠላቴን አስወግድልኝ።
የአንተ ነኝ፥ የአንተ ነኝ፤
እመጣለሁ ተቀበለኝ።
