Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 140 አምላክ ሆይ፥ ማረን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 140 አምላክ ሆይ፥ ማረን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ አምላክ ሆይ፥ ማረን
ፍርድ ሲያስፈራራን፥
ጸጋህን ስጠን፥
ምሕረት አድርግልን።
እኛ አፈር ነን፤
የሚበን ትቢያ
አላፊ ጥላ።
፪፡ የኃጢአት ቀንበር
ከብዶን ስንጨነቅ፥
ምኞትም በዝቶ
ፈተና ሲያስተን፥
ድካም ሲሰማን፥
አንተ ብርታት ሁነን
በፍቅርህ እርዳን።
፫፡ የተሠቃየው
የእሾህ ዘውድ የጫነው፥
ለኛ የሞተው
እኛን ሊያስታርቅ ነው።
ስለ የሱስ ብለህ፥
አምላክ ሆይ ራራልን፤
ምሕረትን ሰጠን።
፬፡ በቅዱስ ደሙ
የወጣ ከጐኑ
እንድናለን።
ይጠጋል ቁስላችን
ቸር እረኛችን።
ዞትር ይጠራናል
ይራራልናል።
፭፡ አምላክ ሆይ እርዳን
ስለ የሱስ ማረን
ሲማልድልን
ጸሎቱን ስማልን።
ይቅር ብለኸን
ልጆችህ አድርገን
አባት ሁንልን።
ተ.ኡሌ ኤሪክሶን

Exit mobile version