Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 139 አምላካዊ ብርሃን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አምላካዊ ብርሃን
ከአርያም፣ ከሰማያት
መንፈስህን ስጠኝ
ልቤን እንዲያበራልኝ።
፪፡ የድሆች አባት ሆይ፥
የጠፋሁኝ ልጅህን
አንተ መልሰኝ
ሰላምህንም ስጠኝ።
፫፡ ከኃጢአቴ ርቄ
ከጥላህ በታች እንዳርፍ፥
ከድካም ሁሉ
በጸጋህ ብርታት ሁነኝ።
፬፡ የዘላለም ብርሃን
አብራልኝ መንገዴን
በሰላም ልኖር
በላይ በሰማይ አገር።
፭፡ ጭው ካለው በረሃ
ወዳንተ መድኃኒቴ
ወደ ጥላህ ስር
ቅዱስ መንፈስህ ይምራኝ።
፮፡ ሕይወቴ ያንተ ነው
ያንተ ነው ሰውነቴ፤
መላው ንብረቴም
ያለኝ ሁሉ ያንተ ነው።
