Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 138 በክርሰቶስ ሞት ተጠምቀናል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 138 በክርሰቶስ ሞት ተጠምቀናል የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ በክርሰቶስ ሞት ተጠምቀናል
ነጽተናል ከኃጢአት
በትንሣኤው ድል ነሥተናል
ሆነልን ታላቅ ሐሴት።
ከወልድ ጋር የተሰቀለው
አሮጌው ሰውነታችን
ተወግዷል በጸጋው
አዲስ ፍጥረት እንድንሆን።
፪፡ በዚህ ጥምቀት ልጅነትን
ሁላችን አግኝተናል።
አምላክ በጸጋው ወለደን
የኃጢአትንም ኃይል
አጠፋልን በልጁ።
በመንፈሱ እንድንኖር
ይመክረናል በቃሉ
ይጠብቀናል በምድር።
፫፡ ተሰጥቶናል መንፈስ ቅዱስ
ሊያነፃን ሊቀድሰን።
ካልተቀደስን በመንፈስ
አይሆንልንም አሁን
ልንኖር በቅድስና።
ቅዱስ አምላክ ይወደናል
ለቅድስና ሥራ
እርሱ ያዘጋጀናል።

Exit mobile version