Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 136 የሱስ ልጆቻችንን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 136 የሱስ ልጆቻችንን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የሱስ ልጆቻችንን
ወዳንተ ስናቀርባቸው፥
አምነን ቅዱስ ተስፋህን
በስምህ ስናጠምቃቸው፥
በፍቅርህ ተቀበላቸው፤
በረከትህንም ስጣቸው።
፪፡ የሱስ ክርስቶስ ያንተ ደም፥
በአብ ፊት ይቀድሳቸው።
መንፈስ ቅዱስ በቃልህ
በሕይወት መንገድ ይምራቸው።
ጽድቅህን ይጎናጸፉ፥
መንግሥትህንም ይውረሱ።
፫፡ ታናናሾች በጎችህ
ከእረኛቸው አይለዩ።
ሁልጊዜ በመንገድህ
ሄደው፥ ካለም ሸር ይዳኑ።
ርስትህ እንዳይቀርባቸው፥
አንተ ራስህ ጠብቃቸው።

Exit mobile version