Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 135 የየሱስ ስም ያጽናናል የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የየሱስ ስም ያጽናናል፤
በመከራም ይረዳናል።
እርሱ ሆኖልናል መድኅን፥
በጸጋው እንኖራለን።
፪፡ ያምላክ ልጅ ሆይ ረድኤታችን፥
በምሕረትህ ይቅር በለን።
ኦ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው፥
ሕይወታችንን ቀድሰው።
፫፡ ጽድቅ የሚገኘው ባንተ ነው፥
እርቅና ሰላም ካንተ ነው።
በቅዱስ ስምህ ያመነ፥
እርሱ ከፍድ ሁሉ ዳነ።
፬፡ ምስጋና ስለ ጥምቀትህ፥
ስለ ቁርባንም እንስጥህ።
በዚህ ዓለም ሰላም ስጠን፥
በሰማይ ቤትም ሰብስበን።
