Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 127 ገስግሶ ሲያልፍ ቀናችን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 127 ገስግሶ ሲያልፍ ቀናችን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ገስግሶ ሲያልፍ ቀናችን
ባምላክ ቃል ሠርክ እንጽና።
እርሱ ነው የሚያበራልን
በዚህ ዓለም ጨለማ።
ከጥንት ዘመን ጀምሮ
ኃይልን ደስታን ሰጥቶ።
ወደ ሰማይ በሚመራ
በዚህ ቃል ዘወትር እንጽና።
፪፡ በዚህ ዓለም ስንዋትት
እንደ ጥንቱ ቅዱሳን።
ቅዱስ ቃሉን ለማዳመጥ
እንሰብሰብ ሲጠራን።
አባት ከልጆቹ ጋር
ያቅርብለት ምስጋና
በምሕረቱ እንዲያየን
ዘወትር ተግተን እንለምን።
፫፡ ባርከነ ጠብቀነ
ጸጋን ሞገስን ስጠን።
ዘወትር በምክርህ ምራነ
በመንገድ ብርሃን ሁነን።
መልስልን ፊትህን
ሰላምህን አካፍለን።
ሥሉስ አምላክ ስለ ፍቅሩ
ይመስገን በዓለም ሁሉ።

Exit mobile version