Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 126 አምላክ ከእናንተ ዘንድ ይሁን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 126 አምላክ ከእናንተ ዘንድ ይሁን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ አምላክ ከእናንተ ዘንድ ይሁን።
ዞትር በቃሉ ይምራችሁ፥
በፍቅሩ ይሸከማችሁ፥
እስክንገናኝ በየሱስ ፊት።
በሰማይ፥ በሰማይ፥
በሰማይ፥ እስክንገናኝ፥
በሰማይ፥ በሰማይ፥
እስክንገናኝ በየሱስ ፊት።
፪፡ አምላክ ከእናንተ ዘንድ ይሁን።
ከጉዳት ይጠብቃችሁ፥
መናን ከሰማይ ይስጣችሁ፥
እስክንገናኝ በየሱስ ፊት።
በሰማይ . . .።
፫፡ አምላክ ከእናንተ ዘንድ ይሁን።
ፈተና ሲያስፈራችሁ፥
በኃይሉ ያጠንክራችሁ፥
እስክንገናኝ በየሱስ ፊት።
በሰማይ . . .።
፬፡ አምላክ ከእናንተ ዘንድ ይሁን።
አትካዱ ዓላማችሁን፥
ሞት እንኳ ቢሆን አትፍሩ፥
እስክንገናኝ በየሱስ ፊት።
በሰማይ . . .።

Exit mobile version