Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 12 ለደስታ ቀን ሆነ ንጋት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 12 ለደስታ ቀን ሆነ ንጋት የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ለደስታ ቀን ሆነ ንጋት
ላለም የምሥራች ሆነላት
መሢሕ እንደ ተወለደ
ለእረኞች ተገለጠ።
፪፡ በደንባሮች በጎች መሐል
በጎ እረኛ ገብቶአል።
የጠፉትን ይፈልጋል
ሰባሮችን ይጠግናል
፫፡ ትሑት ርኀሩኅ ሆኖ መጣ
እኛን ነጻ ሊያወጣ።
በመስቀልም ላይ ሞተልን
የመዳን ኃይል ሊሆንልን።
፬፡ ለጋ ተክል የመሰለች
ቤተ ክርስቲያን ለመለመች
ቅርንጫፎችዋ በዓለሙ
ለደከሙ ያጠላሉ።
፭፡ ዝናም ምድርን እንደሚያርስ
የአምላክም ቃል ያለማል።
ጽድቅና ሰላም ያወርዳል
የሕይወት ፍሬ ይሰጣል።
፮፡ ሰማይና ምድር ያልፋል
የየሱስ ቃል ግን ይኖራል።
አሕዛብ ለእርሱ ሰገዱ
ታላቁን ስሙን ታመኑ።
፯፡ በየሱስ ኃይል ኦ ክርስቲያን
በዚህ ዓለም ላይ ሁን ብርሃን።
የታገለ ድል ይነሣል
የታገሠም ይከብራል።
፰፡ ለቸር አምላክ ይሁን ስብሐት
ስላሳየን ፍቅር ምሕረት።
በምሕረቱም ስላዳነን።
እስከ ዘላለም ይመስገን።

Exit mobile version