Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 115 ወዳምላክ ቤት ገብቻለሁ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ወዳምላክ ቤት ገብቻለሁ
ቅዱስ ቃሉን ለመስማት
በቅን መንፈስ እሰግዳለሁ
በሰማይ ላለው አባት።
እርሱ ጸሎቴን ይሰማል
በረከቱን ይሰጠኛል።
፪፡ ቸር አምላኬ ሆይ ተቀበለኝ
ከኃጢአቴ አንፃኝ
ልቤን አሁን ቀድስልኝ
የአንተ ልጅ አድርገኝ።
ምስጋና እንዳቀርብልህ
አኑረኝ በቅድስናህ።
፫፡ ልቤን አድርግ ፍሬያማ እርሻ
ቃልህ እንዲዘራበት
መልካም ፍሬ እንዲያፈራ
አውርድልኝ በረከት።
ቅዱስ ቃልህን በመስማት
ካንተ ጋር ይኑረኝ ኅብረት።
፬፡ ጌታ እዘዝ እሰማለሁ
ትእዛዝህ ደስ ይለኛል
የሕይወት ውሃ ሲመነጭ
የማይጠጣ ይጠፋል።
ከጭንቀት ሁሉ አድነኝ
በቸርነትህ ጠብቀኝ፡
