Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 11 የደስታ ሌት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 11 የደስታ ሌት የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የደስታ ሌት፥ የሰላም ሌት፥
ጸዳልሽ ያበራል።
እረኞች ብርሃንን አዩ፥
ወደ መድኅን ገሰገሱ።
ሕፃኑን አገኙ፥
ሕፃኑን አገኙ።
፪፡ ቅዱስ ጊዜ፥ ታላቅ ጊዜ፥
ነቢያት ያወጁት፥
ባለም ጨለማ ወጣ ብርሃን፥
ክብር ላምላክ በሰዎች መዳን።
በምደር ሁሉ ሰላም፥
በምደር ሁሉ ሰላም።
፫፡ የደስታ ሌት፥ የሰላም ሌት፥
የመዳን ጊዜ ንጋት፥
ታላቅ መልካም የምሥራች ቃል፥
ክርስቶስ ለኛ ተወልዶአል።
የሱስ የሰላም ንጉሥ፥
የሱስ የሰላም ንጉሥ።

Exit mobile version