Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 107 ወዴት አመልጣለሁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 107 ወዴት አመልጣለሁ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ወዴት አመልጣለሁ
ከአምለኬ ፊት?
ሰው የለም ከርሱ የሚሰወር።
የሚያስፈራራ የፍርድ ቀን ሲደርስ
እንዴትስ ልቁም ያለ ነውር?
እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ።
፪፡ ሽቅብ ብመለከት
ጭንቀት ይይዘኛል፤
ከአርያም ይመጣል ዳኛዬ።
ቁልቁል ብመለከት ያሳፍረኛል
በምድር ተጻፈ ኃጢአቴ።
እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ።
፫፡ የሱስ ሆይ በመስቀልህ
ስለ ፈሰሰው
ሰለ ደምህ ይቅርታ ስጠኝ፤
ለፍርድ ስትመጣ በምሕረትህ
ነፃ አድርገኸኝ አቁመኝ
እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ።

Exit mobile version