Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 105 አምላክህ ለፍርድ ቢመጣብህ አሁን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አምላክህ ለፍርድ
ቢመጣብህ አሁን
ተዘጋጅተህ ትገኝ ይሆን ወይ?
የፍርድ መለከትስ ቢነፋ አሁን?
ምን አሳብ ይይዝህ ይሆናል?
እንዴትስ ያን ድምጽ ትሰማለህ?
፪፡ ባላሰብኸው ወቅት
በማይመስልህ ሰዓት
ያ ቀን እንደ ሌባ ይመጣል።
ለጻድቃን ደስታ ለኃጥአን ፍርሃት፥
ጌታችን በፍርዱ ይሰጣል።
ላንተስ ምን ይሰጥህ ይሆናል
፫፡ በጎችን በቀኝ
ፍየሎችን በግራ
አድርጎ መንጋውን ይለያል።
አንተንስ ከበጎቹ ጋራ ይጥራ
ወይስ ስፍራህን የት ላይ ያሳያል?
በየት ትቆማለህ በፍርዱ?
፬፡ በጎቹን በፍቅር
እናንተ ቡሩካን
እያለ በገነት ያስገባል።
ለኃጥአን ግን ሂዱ እናንተ ርጉማን
ብሎ መቅሠፍታቸውን ይሰጣል
አንተንስ ምን ይልህ ይሆናል
፭፡ ካምላከህ ጋር
ልትገናኝ ተዘጋጅ
የሱስን ለማወቅ ተጋደል።
አሁን ለሁላችን ምሕረቱን ሲሰጥ
ጊዜ ሳያልፍብህ ተቀበል
የጸጋን ጊዜ አታባክን።
